=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
• አሰላሙ አለይኩም__ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው ሲገናኙ የሚለዋወጡት ሰላምታ ሲሆን ትርጉሙም «ሰላም ባንተ ላይ ይሁን» ማለት ነው።
• አሲዲቅ__ እውነተኛ/ሃቀኛው
ይህ መጠሪያ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ለአቡበክር የተሰጡት ነው።
• አሹራ__ የሙሐረም ወር አስረኛ ቀን ነው።
ይህ ቀን አሏህ ሙሳንና የኢስራኤል ልጆችን ከፊርአውን የጠበቀበት ቀን ነው።
• አኡዙ ቢላሂ ሚነሸይጧኒ ረጂም__ አንድ ሙስሊም ቁርአን ከማንበብ በፊት ፣ ከመናገሩ ፣ ዱአ ከማድረጉ በፊት ፣ ወደ መፅዳጃ ቤት ከመግባቱ በፊት እና ማንኛውንም ነገር ከማከናወኑ በፊት የሚለው አረፍተ ነገር ሲሆን ትርጉሙም «ከተረገመው ሸይጧን በአሏህ እጠበቃለሁ» ማለት ነው።
• አውልያ__ ጓደኛ/ረዳት/ደጋፊ
• አውራህ__ ሐፍረተ ገላ
• አያህ__ ታአምር/ምልክት
• አያት__ ታአምራት
• አያቱል ኩርሲይ__ ሱራ አል-በቀራ አያህ 256 አያቱል ኩርሲይ ተብሎ ይጠራል
• አዝዋጅ__ጥንዶች(ባልና ሚስት)
• ባበልሪያን__ አንደኛው የጀነት መግቢያ በር ስም ነው።
• በድር__ በሙስሊሞችና በአሏህ ጠላቶች መካከል የተካሄደ የመጀመሪያው ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ(ጦርነት) ነው።
=>ይህ ጦርነት የተካሄደው በሁለተኛው ዓመተ ሂጅራ በሙስሊሞችና በመካ ቁረይሾች መካከል ነበር። በድር የምትገኘው ከሚዲነቱል ሙነወራ በስተደቡብ 150 ርቃ ነው። የሙስሊም ወታደሮች ቁጥር 313 ሲሆን የቁረይሽ ወታደሮች ደግሞ 1000 ነበሩ።
• በይቱሏህ__የአሏህ ቤት
• በይቱል ሃምድ__የምስጋና ቤት
• በካ__የመካ ሌላኛ መጠሪያ ስም ነው።
• በኒ ኢስራኢል__ የእስራኤል ጐሳ
• ባረከ ሏህ__ የአሏህ በረካ ባንተ ላይ ይሁን
=> አንድ ሙስሊም አንድን ሰው ሲያመሰግንና ውለታን ሲመልስ ይህን አባባል ይጠቀማል። ሰው የውየውም «ባረከ ሏህ ፊኩም» ብሎ ይመልስለታል።
• በርዘህ__በምድር ህይወትና በአሂራ ሂወት መካከል ያለ ክፍል
• ባቲጢል__ ውሸት/ውሸታም
• ቢንት__ ሴት ልጅ
• ቢስሚላህ__በአሏህ ስም
• ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም__ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
• ቡህታን__ ሃሜት
• ቡራቅ__ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ ሚእራጅ የተጓዙበት እንሰሳ
• በስር__በከፊል የበሰለ ተምር
• ኸሊፋ__ ወራሽ/ተተኪ
• ደህሪ__ እምነት አልባ
• ደጃል__ውሸታም/አታላይ
መሲኸ ደጃል በመባልም ይታወቃል።
• ደሊል__ ማረጋገጫ/ማስረጃ
• ዶላል__ ጥመት
• ዳእዋ__ ጥሪ ወደ ኢስላም
• ዚክር__ አሏህን ማስታወስ
• ዙል ሂጃ__በሙስሊሞች የቀናት አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው ወር ነው።
• አዲኑል ፊጥራ__ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሃይማኖት(ዲነል ኢስላም)
• ዱአ__ ፀሎት
• ደንክ__የውመል ቂያማ ካፊሮች አይነአማ ሁነው የሚቀሰቀሱበት
• ዱንያ__ ምድራዊ አለም
• ኢድ__ በዓል
=>በእስልምና ሁለት ዋና በአሎች አሉ።
1) ኢዱል ፊጥር
2) ኢደል አድሃ
• አል-ፋቲሃ__ መክፈቻ
የቁርአን የመክፈቻ ምእራፍ
• ፋሩቅ__ ይህ ስም የተሰጠው ለዑመር ኢብን አልኸጧብ ነበር። ትርጉሙም እውተትን ከውሸት የሚለይ ማለት ነው።
• ፊ ሰቢሊላህ__ በአሏህ መንገድ
• ፊርደውስ__ የጀነት መካከለኛና ከፍተኛው ክፍል
• ገዝዋ__ ጦርነት/ወታደራዊ ዘመቻ
• ጉስል__ የገላ ትጥበት
• ሐፍሳ__ የዑመር ኢብን አልኸጧብ ሴት ልጅ ፤ የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ሚስት ነበሩ።
• ሀፊዝ__ ቁርአንን የሸመደደ
• ሃይድ__ የወር አበባ
• ሃጀረል አስወድ__ ጥቁር ድንጋይ
• ሃኪሚያ__ ሉአላዊነት
• ሃና__ የነብዩ ሏህ ኢሳ(ዐ.ሰ) ሴት አያት
• ሀሰን__ መልካም/የሚያምር/ የሚደነቅ
• ሐዋ__ የአደም(ዐ.ሰ) ሚስት
• ሂዳያ__ መመሪያ(ከአሏህ)
• ሂማ__ ጥብቅ ደን
• ሁድና__ የጦር አቁም ስምምነት
• ሁዱድ__ ገደብ
• ሁጃጅ__ ሀጅ የሚያደርግ ሰው
• ሁክም__ፍርድ
• ኢማም__ ሃይማኖታዊ መሪ/የጀምአ ሶላትን የሚመራ
• ኢማሙል ሙርሰሊን__ የመልዕክተኞች መሪ
• ኢምላስ__ ከሆድ አካባቢ በመመታት ምክኒያት ማስወረድ
• ኢህቲላፍ__ አለመግባባት/የሀሳብ ልዩነት/ጭቅጭቅ
• ሂራ__ በመካ አቅራቢያ ያለ የቦታ ስም ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህን በብቸኝነት ለመገዛት ወደዚህ ቦታ ይሄዱ ነበር። እዚህም ቦታ ነበር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያውን ወህይ(ራዕይ) የተገለፀላቸው።
• ኢላህ__ አምላክ/ጌታ
• ኢምሳክ__ የፆም ጊዜ መድረስ(መጀመር)
• ኢንጅል__ በነብዩ ሏህ ኢሳ(ዐ.ሰ) ዘመን የተላከ ወህይ(ራዕይ)
• ኢንስ ወል ጂን__ የሰው ልጅና ጅኒ
• ኢንሳን__ ሰው/የሰው ልጅ
• ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅኡን__ አንድ ሙስሊም መጥፎ ነገር ሲያጋጥመው ፣ የሚወዳቸውን ሰዎች ሲያጣ ፣ ኪሳራ ሲደርስበት ፣ መሰናክሎች ሲያጋጥሙት ሶብር በማድረግ ይህን አባባል (አረፍተነገር) ሊል ይገገባል። ትርጉሙም እኛ ለአሏህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን
• ኢንሻ አሏህ__ አሏህ ከፈቀደ(ካሻ)
• ኢቃመት አሶላት__ ትክክለኛና ሙሉ በሆነ መልኩ ሶላትን መስገድ
• ኢስላም__ ሲልም ወይም ሰላም ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ሰላም ፣ ታዛዥነት ወይም ለአሏህ ፈቃድ ራስን ማስገዛት ማለት ነው።
• ኢስነድ__ የእያንዳንዱ ሐዲስ የዘገባ ሰንሰለት
• ኢስራ__ የምሽት ጉዞ
• ኢስቲግፋር__ የአሏህን ምህረት መሻት
• ኢስቲኻራ__ ሃያሉ አሏህ ቀናውን መንገድ እንዲመራህና ችግሮችህን እንዲያቃልልህ መለመን
• ኢስቲንጃ__ የብልት ክፍሎችን በውሃ ማፅዳት
• ኢስቲስቃ__ በድርቅ ወቅት አሏህ(ሱ.ወ) ዝናብ ይሰጠን ዘንድ መለመን
• ኢቲሃድ__ ማንነት/ህብረት
• ጀመአ__ ግሩፕ
• ጃሂልያ__ ድንቁርና/በድንቁርና ፅልመት ውስጥ ያለ
• ጃህል__ ድንቁርና/እብሪተኝነት
• ጃህሪ__ በሶላት ወቅት ድምፅን ከፍ አድርጎ ቁርአን መቅራት
• ጀለሰ__ ተቀመጠ
• ጀናዛ__ አስክሬን/የቀብር ስነስርአት
• ጀዛከሏህ ኸይር__ አሏህ በመልካም ነገር ይመንዳህ
• ጂን__የተሰወረ
• ጁሁድ__ መካድ
• ጃሂድ__ ከሃዲ
• ካሚል__ ፍፁም የተሟላ/ሙሉ
• ከባኢር__ ትልቅ
• ከባኢረዙ ኑብ__ትልቅ ሃጢያት
ለምሳሌ:-
1) ሽርክ(ማጋራት)
2) ግድያ
3 ስርቆት
4) ዝሙት ዘ.ተ
• ከላም__ ንግግር
• ከላሙ ሏህ__ የአሏህ ንግግር
• ኸሊዲን__ዘውታሪ
• ኸሊዲነፊሃ አበዳ__ በውስጧም ለዘላለም ይኖራሉ(ዘውታሪዎች ይሆናሉ)።
• ሃሊቅ__ፈጣሪ
• ኸልቅ__ የአሏህ ፍጥረት
• ኸምር__ የአልኮል መጠጥ
• ኢጅተኒቡ__ ተውት
• ኸንደቅ__ ጉድጓድ/ጉድባ
• ሃተመን ነብይ__ የነብያቶች መደምደሚያ
• ሃጢብ__ ተናጋሪ
• ኸውፍ__ ፍርሃት
• ሁሹእ__ አትኩሮት/ራስን ዝቅ ማድረግ
• ኩን__ ሁን
• ኡም__ እናት
• አብ__ አባት
• ላ ሃውለውላ ቅወተ ኢላ ቢላህ__ ሀይልም ብልሃትም የለም ከአሏህ ቢሆን እንጂ።
• ላኢላሃ ኢለሏህ__ ከአሏህ ውጭ ሊያመልኩት የሚገባ ነገር የለም።
• ሙሐመድ ረሱሉ ሏህ__ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ ናቸው።
• ላእና__ እርግማን
• ለይለቱል ቀድር__ የሃይል ምሽት/የእድል ምሽት
• ሉቅማን__ የጥንት አረቢያ ጠቢብ ሲሆን ሙአመር(ለረጅም ጊዜ የኖረ) የሚል መጠሪያም አለው።
• መድረሳ__ ትምህርት ቤት
• መግፊራ__ ምህረት
• መሃባ__ ውዴታ
• መህር__ ጥሎሽ
• መይስር__ ቁማር
• መክሩህ__ የተጠላ
• መቃሲድ__ አላማ/ግብ
• መሳኪን__ ችግረኞች
• መዲነተ አነበውይ__ የነብዩ ከተማ
• ሙእጅዛት__ ተአምራት
• ሙህሰናት__ የተጠበቀች ሴት
• ሙበሽራት__ የምስራች/የደስደስ
• ሙፍሪድ__ አሏህን አዘውትሮ የሚያወሳ
• ሙሐዲስ__ የሐዲስ ሊቅ
• ሙሐዲሲን__ የሐዲስ ሊቃውንት
• ሙሃጅር__ ስደተኛ
• ሙእሚን__ በአሏህ ጥልቅ ኢማን ያለው
• ሙሽሪክ__ ጣኦት አምላኪያን/አጋሪዎች/የሽርክ ሰዎች
• ሙስሊም__ ራሱን ለአሏህ ፈቃድ ተገዥ ያደረገ
• ነፍስ__ ሩህ
• ነህኑ__ እኛ
• ነህር__እርድ
• ናር__ እሳት
• ናቂብ__ የጐሳ መሪ/በዘመቻ ጉዞ ላይ ያሉ ሰዎች መሪ
• ናስ__ የሰው ልጅ
• ሙተቁን__ አሏህን የሚፈሩ ሰዎች
• ነሷራ__ ለክርስቲያን እምነት ተከታዮች የተሰጠ መጠሪያ ስም ነው።
• ኒካህ__ ጋብቻ
• ኑን__ አሳ
• ኑቡዋ__ ነብይነት
• ኑር__ ብርሃን
• ኑዙል__ የቁርአን ወህይ(ራዕይ)
• ቀዷ ወ ቀድር__ ድንጋጌና እጣፈንታ/እድል
• ቃዲ__ ዳኛ
• ቀለም__ እስክርቢቶ
• ቀልብ__ ልብ
• ቀመር__ ጨረቃ
• ቃሪ__ ቁርአን የሚቀራ ሰው
• ቂል ወቃል__ እንቶ ፈንቶ ወሬ
• ቂብላ__ አቅጣጫ
• ቂታል ፊሰቢሊላህ__ በአሏህ መንገድ መታገል(መፋለም)
• ቂያም__ መቆም
• ቂያማ__ ትንሳኤ
• ቂያሙ ለይል__ ለሊት ለሶላት መቆም
• ረብ__ ጌታ/አምላክ
• ረበክ__ ጌታህ
• ረበል አለሚን__ የፍጥረታት ጌታ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|